Minnesota Secretary Of State - ድምጽ ለመስጠት ይመዝገቡ (Register to Vote)
Skip to main content

ድምጽ ለመስጠት ይመዝገቡ (Register to Vote)


በዚህ ገጽ ላይ ማን መምረጥ እንደሚችል እና ከምርጫ ቀን በፊት ወይም በዛው ቀን እንዴት እንደሚመዘገቡ ይወቁ።

ማን መምረጥ ይችላል?

በሚኒሶታ ውስጥ ድምጽ ለመስጠት የዩኤስ ዜጋ፣ በምርጫ ቀን ቢያንስ 18 አመት መሆን እና ቢያንስ ለ20 ቀናት በሚኒሶታ ነዋሪ መሆን አለብዎት።

በሚኒሶታ ውስጥ እንደ 16 እና 17 አመት ልጅ ለመምረጥ አስቀድመው መመዝገብ ይችላሉ። ድምጽ ከመስጠትዎ በፊት 18 አመት መሆን ይጠበቅብዎታል።

በወንጀል ጥፋተኛነት ያለብዎት ከሆነ፤ ለዚያ ጥፋተኛነት እስረኛ ካልሆኑ ድምጽ መስጠት ይችላሉ።

ዳኛ የመምረጥ መብትዎን ካላነሳ በስተቀር በጥበቃ ውስጥ ሆነው ድምጽ መስጠት ይችላሉ።

የምዝገባ መመሪያዎች

አሁን ባሉበት አድራሻ ድምጽ ለመስጠት መመዝገብ ይጠበቅብዎታል። ድምጽ ለመስጠት ይመዝገቡ ወይም የወረቀት ማመልከቻን በ አማርኛ ያትሙ

እንዲሁም በምርጫ ቀን በምርጫ ቦታዎ መመዝገብ ይችላሉ። የስምህን እና የአሁን አድራሻህን ማረጋገጫ ማሳየት አለብህ።

ከተንቀሳቀስኩ ወይም ስም ከቀየርኩ መመዝገብ አለብኝ?

አድራሻዎን ሲቀይሩ፣ ስምዎን በሚቀይሩበት በእያንዳንዱ ጊዜ እንደገና መመዝገብ አለብዎት ወይም በአራት አመት ጊዜ ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ ድምጽ አይስጡ፡፡ አዲስ የምዝገባ ማመልከቻ በማጠናቀቅ ምዝገባዎን ያዘምኑ።

በምርጫ ቀን እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል

በምርጫ ቀን በምርጫ ቦታዎ ለመመዝገብ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት አንድ የመኖሪያ ማረጋገጫ ይዘው ይምጡ።

1. መታወቂያ አሁን ካለዎት ስም እና አድራሻ ጋር

  • ህጋዊ የሚኒሶታ መንጃ ፍቃድ፣ የተማሪ ፍቃድ ወይም መታወቂያ፣ ወይም ከእነዚህ ውስጥ ለማንኛውም ደረሰኝ፡፡
  • ስም፣ አድራሻ፣ ፎቶ እና ፊርማ ያለው የጎሳ መታወቂያ።

2. የፎቶ መታወቂያ እና የአሁኑ ስምዎ እና አድራሻዎ ያለው ሰነድ

የጸደቁ የፎቶ መታወቂያዎች (አንዱን ይምረጡ)
ጊዜው ያለፈበት ሊሆን ይችላል፡፡

  • በማንኛውም ግዛት የተሰጠ የመንጃ ፈቃድ፣ የግዛት መታወቂያ ወይም የተማሪ ፈቃድ
  • የዩኤስ ፓስፖርት
  • የዩኤስ ወታደራዊ ወይም የአርበኞች መታወቂያ
  • የጎሳ መታወቂያ ከስም ፣ ፊርማ እና ፎቶ ጋር
  • የሚኖሶታ ዩኒቨርሲቲ፡ የኮሌጅ ወይም የተግባረ እድ ኮሌጅ የመታወቅያ ወረቀት
  • የሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጅ ወይም የቴክኒክ ኮሌጅ መታወቂያ

የተፈቀዱ ሰነዶች (አንዱን ይምረጡ)
በኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ላይ ሊታዩ ይችላሉ፡፡

  • በምርጫው ቀን ወይም በ30 ቀናት ውስጥ የሚከፈል ቢል፣ አካውንት ወይም የአገልግሎት ጅምር መግለጫ፡
    • ስልክ፣ ቲቪ ወይም ኢንተርኔት
    • ደረቅ ቆሻሻ፣ ፍሳሽ፣ ኤሌክትሪክ፣ ጋዝ ወይም ውሃ
    • የባንክ ወይም የክሬዲት ካርድ
    • የቤት ኪራይ ወይም ብድር
  • በምርጫ ቀን የሚሰራ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ወይም የኪራይ ውል
  • ወቅታዊ የሆነ የተማሪ ክፍያ መግለጫ

3. አድራሻዎን ማረጋገጥ የሚችል የተመዘገበ መራጭ

ከአከባቢዎ የተመዘገበ መራጭ ከእርስዎ ጋር ወደ ምርጫ ቦታው በመሄድ አድራሻዎን የሚያረጋግጥ መሃላ ሊፈርም ይችላል። ይህ ‘ቫውቺንግ’ በመባል ይታወቃል። የተመዘገበ መራጭ እስከ ስምንት መራጮች ድረስ ለእጩነት ሊጠቁም ይችላል። አንድ ሰው ለእርስዎ ከጠቆመ ለሌሎች ጥቆማ መስጠት አይችሉም።

4. የኮሌጅ ተማሪ መታወቂያ ከቤቶች ዝርዝር ጋር

ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ አስፈፃሚዎችን የተማሪ መኖሪያ ቤት ዝርዝር ይልካሉ፡፡ በዝርዝሩ ውስጥ ካሉ፣ ምዝገባዎን ለማጠናቀቅ የኮሌጅ ፎቶ መታወቂያዎን ያሳዩ።

5. ትክክለኛ ምዝገባ በአውራጃው

በአውራጃው ውስጥ የተመዘገቡ ነገር ግን ስሞችን ከቀየሩ ወይም በዚያው አውራጃ ውስጥ ከተዛወሩ፤ የቀድሞ ስምዎን ወይም አድራሻዎን ብቻ ለምርጫ ዳኛ መንገር ያስፈልግዎታል።

6. የዘገየ ምዝገባ ማስታወቂያ

በምርጫው በ20 ቀናት ውስጥ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገቡ፣ የዘገየ የምዝገባ ማስታወቂያ በፖስታ ሊያገኙ ይችላሉ። ከእርስዎ ጋር ይዘው ይምጡ እና ለመመዝገብ እንደ የኗሪነት ማረጋገጫዎ ይጠቀሙበት።

7. የመኖሪያ ተቋም ሰራተኛ ሰው

በመኖሪያ ተቋማት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ አንድ ሰራተኛ አድራሻዎን ለማረጋገጥ ወደ ምርጫ ቦታ ከእርስዎ ጋር መሄድ ይችላል፡፡ ይህ ‘ቫውችንግ’ በመባል ይታወቃል። አንድ ሰራተኛ በተቋሙ ውስጥ ለሚኖሩ ሁሉም ብቁ መራጮች ማረጋገጫ ሊሆን ይችላል።