በሚኒሶታ ውስጥ፣ የምርጫ ቀን እስኪደርስ ድረስ መጠበቅ አይኖርብዎትም - በፖስታ ወይም በአካባቢዎ የምርጫ ቢሮ ቀደም ብለው ድምጽ ይስጡ!
ከምርጫ ቀን 46 ቀናት በፊት ጀምሮ በአከባቢዎ ምርጫ ቢሮ በየቀሪ ድምጽ መስጫ መምረጥ ይችላሉ።
እንዲሁም የቀሪ ድምጽ መስጫ በፖስታ እንዲላክልዎ ማመልከት ይችላሉ። የምርጫ ካርድዎን በምርጫ ቀን መመለስ አለቦት።
ድምጽ ሲሰጡ እና ድምጽ መስጫዎን ሲያጠናቅቁ ምስክር ያስፈልግዎታል። ምስክሩ በሚኒሶታ የተመዘገበ መራጭ ወይም ኖታሪ ሊሆን ይችላል። ምስክርዎ የፊርማ ፖስታውን መፈረም እና አድራሻቸውን መዘርዘር አለባቸው።
ለመምረጥ ካልተመዘገቡ፣ በቁሳቁሶችዎ ውስጥ የምዝገባ ማመልከቻ ያገኛሉ፡፡ ለመመዝገብ፣ ምስክርዎን ያሳዩ አንድ የመኖሪያ ማረጋገጫ፡፡ ምስክርዎ በፊርማ ፖስታዎ ላይ የትኛውን መታወቂያ እንዳሳዩዋቸው ምልክት ማድረግ አለበት።
በወቅቱ የደረሱ እና ቅጾቹ በትክክል የተሞሉ ሁሉም የቀሪ ድምፅ መስጫዎች ይቆጠራሉ።
የድምጽ መስጫዎትን ሁኔታ ይከታተሉ እና መድረሱንና መቆጠሩን ያረጋግጡ፡፡