ወደ ሚኖሶታ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የንግድ አገልግሎት እንኳን በደህና መጡ!
ወደ ሚኖሶታ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የንግድ አገልግሎት እንኳን በደህና መጡ!
ዋናው ዓላማችን በዚህ የንግድ ስራ ለማካሄድ ምቹ በሆነው ክፍለሃገራችን ውስጥ፤ የሚኖሶታ ኗሪዎች፤ ኤኮኖሚያችን በሚሰጣቸው ዕድሎች እንዲጠቀሙና በንግድ ስራ እንዲሳተፉ የሚያስችላቸውን አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ነው።
በዚህ ሳይት (site) የሚከተሉትን እንዴት ማድረግ እንደምትችሉ እናሳያለን፤
• የንግድ ስራዎን ማስመዝገብ
• የንግድ ስራ ማመልከቻዎን መቀየር ወይም ማሳደስ
• ስለ ማንኛውም የንግድ ስራ መረጃ ማግኘት
ከዚህም የበለጠ እናደርጋለን!
አንዳንዱ መረጃ በብዙ ቋንቋዎች የተዘጋጀ ነው። ወደፊትም የቋንቋዎቹ ቁጥር እየጨመረ ይሄዳል።
ሚኖሶታ ውስጥ የንግድ ስራ በሚያካሂዱበት ወቅት፤ ይህ መረጃ ጠቃሚ እንዲሆንሎ ተስፋ አደርጋለሁ። ስላሎት አጠቃላይ አስተያየትና አገልግሎታችንን እንዴት ማሻሻል እንደምንችል አስተያየትዎን ይለግሱን።
ስቲቭ ሳይመን (Steve Simon)
የሚኖሶታ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር (Minnesota Secretary of State)
- በሚኖሶታ ውስጥ የንግድ ስራ እንዴት መጀመር እንደሚቻል
- ሂሳብ (ACCOUNT) መክፈት እንዴት እንደሚቻል
- የንግድ አገልግሎቶች መረጃ ከ ሚኖሶታ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠ
- የማመልከቻዎችና የምስክር ወረቀቶች ቅጂ ለማግኘት እንዴት እንደሚቻል
- ህጋዊ ማረጋገጫ (Apostille) እንዴት ማግኘት እንደሚቻል
- ጠቃሚ የባለቤትነት መረጃ ሪፖርት የማድረግ አዲስ የማእከላይ መንግስት መስፈርት (BOI)